Featured

Welcome to Lubna kids Corner Blog’s

ልጆች የ አላህ(ሱ.ወ) ስጦታ ናቸው።

— Lubna kids corner

Lubna kids’ corner provides helpful researches regarding child education; organize conferences, family festivals and although it introduces young adult Ethiopians to graphics design, programming and other emerging technologies.

ከሉቅማን ምዕራፍ የሚወሰዱ 4 ምክሮች!


አላህ(ሱ.ወ) በቁርዐን ላይ የጠቢቡ ሉቅማንን ምክሮች አስቀምጦልናል! ከእነዚህ ምክሮች መሀል 4ቱን ምክሮች ወላጆች ልጆቻቸውን ያስተምሩበት ዘንድ በዚህ መልኩ አስቀምጠናቸዋል።

1.አላህን በብቸኝነት እንዲገዙ አስተምሯቸው!
“ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን፦ ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን) አታጋራ፤ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና ያለውን (አስታውስ)።”[31፥ 13]
2.ለወላጆቻቸው በጎ እንዲያደርጉ፤ አላህን እና ወላጆቻቸውን ላደረጉላቸው መልካም ነገር ማመስገን እንደሚገባቸው አስተምሯቸው።
“ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ ) በጥብቅ አዘዝነው፤ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው፤ ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው፤ ለኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት (አዘዝነው)፤ መመለሻው ወደኔ ነው።” [31፥ 14] 
3.አላህ ሁሉን አዋቂ እንደሆነና እንደሚቆጣጠረን አስተምሯቸው!
“(ሉቅማንም) አለ ፦ ልጄ ሆይ! እርሷ የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ብትሆንና በቋጥኝ ውስጥ ወይንም በሰማያት ውስጥ ወይንም በምድር ውስጥ፣ ብትሆን፣ አላህ ያመጣታል፤ አላህ ርኅሩኅ ውስጥ ዐዋቂ ነውና።” [31፥ 16]
4.ሰላትንም እንዲሰግዱ አስተምሯቸው።
“ልጄ ሆይ! ሰላትን አስተካክለህ ስገድ፤ በበጎ ነገርም እዘዝ፤ ከሚጠላም ሁሉ ከልክል፤ በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገሥ፤ ይህ በምር ከሚይያዙ ነገሮች ነው።” [31፥ 17] *********
ሀሳብ እና አስተያይትዎን ያጋሩን!
*********
ይወዳጁን!
telegram – https://t.me/lubnakids1
facebook – fb.me/lubnakids1
Instagram – https://www.instagram.com/lubnakidscorner/
Blog – https://lubnakidscorner.wordpress.com


7 ጥቆማዎች ቁጡ እና ለጥል የሚጋበዙ ህፃናት ላላቸው ወላጆች!

ቁጣ የሰው ልጆችን ወደ መጥፎ ለመጎትጎት ሸይጣን የሚጠቀምበት መንገድ መሆኑን መልዕክተኛው ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ለተከታዮቻቸው አስተምረዋል። የቁጣን በሽታነት ከመግለፃቸው ጋር አብሮ መፍትሄዎችን እና መድሀኒቱንም እኒው ተወዳጅ ነብይ ደጋግመው ተናግረዋል። አቡ ሁረይራ በዘገቡት ሀዲስ ላይም አንድ ሰው ወደ እርሳቸው መቶ “ምከረኝ!” እያለ ሲጠይቃቸው ተደጋጋሚ መልሳቸው “አትቆጣ!” የሚል ነበር።[ቡኻሪ፥ ፈትሁል ባሪ 10/456]
በሌላ ዘገባም ላይ ይህ መልዕክተኛውን ምክር የጠየቃቸው ግለሰብ እንዲህ ማለቱ ተዘግቧል። “መልዕክተኛው ስለመከሩኝ ነገር አሰብኩኝና እንደ ቁጣ ሁሉንም ነገር የሰበሰበ መጥፎ ነገር እንደሌለ ተገነዘብኩኝ።” [ሙስነድ ኢማም አህመድ 5/373]
ታድያ ልጆቼ በሚቆጡ ግዜ ምን ላርግ የሚል ጥያቄ ገብትዎታል? 
ውድ ወላጆች እነዚህ ጥቆማዎች ልጅዎ በተናደደ እና ለፀብ በሚጋበዝ ግዜ ሊተገብሯቸው የሚችሉ እና መልካም ውጤትን ሊያመጡ የሚችሉ ጥቆማዎች ናቸው። ጥቆማዎቹ ከማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ከመካነ ድሮች እና ከመፅሀፍት የተውጣጡ ናቸው።
1. ከሸይጣን ጉትጎታ በአላህ(ሱ.ወ) እንዲጠበቁ አስታውሷቸው።
“አንድ ሰው በተናደደ ግዜ ‘ከሸይጣን ጉትጎታ በአላህ እጠበቃለው!’ ካለ ቁጣው ይጠፋል።” ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)!
2. ዝም እንዲሉ በተረጋጋ መንፈስ ይንገሯቸው።
“ከእናንተ መሀል አንደኛቹ በተናደደ ግዜ ዝም ይበል።” ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)!
3. እንዳይንቀሳቀስ አድርጉት ይልቅስ ያለበትን ሁኔታ እንዲቀይር አድርጉት።
“አንደኛቹ በተናደዳቹ ግዜ ቁጣቹ እንዲጠፋ ቆማቹ ከነበረ ተቀመጡ እንዲህም ሆኖ ለውጥ ከለሌ ጋደም ይበል።” ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)!
4. የቁጣቸውን መንስኤ ተረዱና አፅድቁላቸው።
በ Raising Our Children, Raising Ourselves መፅሀፍ ላይ የቁጣ ዋነኛው መንስኤ አጋዥ የማጣት እንደሆነ ተገልፅዋል። በዚው መፅሀፍ ላይ የወላጆች የበዛ ቁጥጥር እና ክልከላም የህፃናቱ የቁጣ መንስኤ መሆኑ ከመገለፁ በላይ ወላጆች የልጆቻቸው ቁጣ ምክንያት የእነርሱ ከሆነ ስህተታቸውን አምነው ይቅርታ ይጠይቋቸው። 
ህፃናት ከህፃናት ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት የሚቆጡት ደግሞ ስሜታቸውን መግለፅ የማይችሉበት ሁኔታ ሲፈጠር መሆኑ ተገልፅዋል። ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ልጅዎ ስሜቱን እንዲገልፅ ገፋፉት።
5. ከተረጋጉ እና ቁጣቸውን ካበረዱ ጀነትን እንደሚቀዳጁ አስታውሷቸው፤ ሌሎች ሽልማቶችንም እንደምትሰጧቸው ንገሯቸው።
ቀደም ባሉ ግዜያት ልጆቻችንን ስለ ጀነት እና ፀጋዎቿ ካስተማርናቸው፤ ልባቸውም በእርሷ እንዲጓጓ ካደረግናቸው በተናደዱ ግዜ እንዲረጋጉ ታላቁ መልዕክተኛ “አትቆጡ! ካልተቆጣቹ ጀነት የእናንተ ትሆናለች ።” ማለታቸውን አስታውሷቸው!
ፕሮፌሰር ያሲር ካንድመር በፃፉት እና ወደ አማርኛ በ ተተረጎመው 40 ሀዲስ ለልጆች ከታሪክ ጋር በሚለው መፅሀፍ ላይ በተጠቀሰ ታሪክ ውስጥ የህፃናትን ቁጣ ለመቆጣጠር አንዲት እናት ልጅዋን ሽልማት እንዳዘጋጀችለት እና ሽልማቱን የሚያገኘው ሲረጋጋ መሆኑን በመግለፅዋ ልጅዋ ራሱን ተቆጣጥሮ ከቁጣ ሲርቅ ተገልፅዋል። ይህን መንገድ እርሶም ይጠቀሙ! ለልጆችዎም ይህን መፅሀፍ በመግዛት ግብረ ገብን ከታሪክ ጋር አንድ ላይ በማድረግ ያስተምሯቸው።
6. ልጆችዎ በተናደዱ ግዜ ለሚናገረው ነገር በእርጋታ ሳይቆጡ ይመልሱለት።
7. የልጅዎን ፍላጎት ይረዱና የእርሶን ፍላጎት በግልፅ ይናገሩ።
በዚህ ግዜ ከሚናገሩት ነገር እኩል የሚናገሩበትንም መንገድ ትኩረት ያድርጉ! ለምሳሌ “ልጄ እንደተናደድክ አውቅያለው። ግን በመናደድ የሚሆን ነገር የለም! ……………..” ይበሉት።
*********
ሀሳብ እና አስተያይትዎን ያጋሩን!
*********
ይወዳጁን
telegram – https://t.me/lubnakids1
facebook – fb.me/lubnakids1
Instagram – LUBNAKIDSCORNER

Design a site like this with WordPress.com
Get started