ከሉቅማን ምዕራፍ የሚወሰዱ 4 ምክሮች!

አላህ(ሱ.ወ) በቁርዐን ላይ የጠቢቡ ሉቅማንን ምክሮች አስቀምጦልናል! ከእነዚህ ምክሮች መሀል 4ቱን ምክሮች ወላጆች ልጆቻቸውን ያስተምሩበት ዘንድ በዚህ መልኩ አስቀምጠናቸዋል። 1.አላህን በብቸኝነት እንዲገዙ አስተምሯቸው! “ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን፦ ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን) አታጋራ፤ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና ያለውን (አስታውስ)።”[31፥ 13] 2.ለወላጆቻቸው በጎ እንዲያደርጉ፤ አላህን እና ወላጆቻቸውን ላደረጉላቸው መልካም ነገር ማመስገን እንደሚገባቸው አስተምሯቸው። “ሰውንም በወላጆቹ (በጎ …

7 ጥቆማዎች ቁጡ እና ለጥል የሚጋበዙ ህፃናት ላላቸው ወላጆች!

ቁጣ የሰው ልጆችን ወደ መጥፎ ለመጎትጎት ሸይጣን የሚጠቀምበት መንገድ መሆኑን መልዕክተኛው ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ለተከታዮቻቸው አስተምረዋል። የቁጣን በሽታነት ከመግለፃቸው ጋር አብሮ መፍትሄዎችን እና መድሀኒቱንም እኒው ተወዳጅ ነብይ ደጋግመው ተናግረዋል። አቡ ሁረይራ በዘገቡት ሀዲስ ላይም አንድ ሰው ወደ እርሳቸው መቶ “ምከረኝ!” እያለ ሲጠይቃቸው ተደጋጋሚ መልሳቸው “አትቆጣ!” የሚል ነበር።[ቡኻሪ፥ ፈትሁል ባሪ 10/456]በሌላ ዘገባም ላይ ይህ መልዕክተኛውን ምክር የጠየቃቸው …

Design a site like this with WordPress.com
Get started