ከሉቅማን ምዕራፍ የሚወሰዱ 4 ምክሮች!


አላህ(ሱ.ወ) በቁርዐን ላይ የጠቢቡ ሉቅማንን ምክሮች አስቀምጦልናል! ከእነዚህ ምክሮች መሀል 4ቱን ምክሮች ወላጆች ልጆቻቸውን ያስተምሩበት ዘንድ በዚህ መልኩ አስቀምጠናቸዋል።

1.አላህን በብቸኝነት እንዲገዙ አስተምሯቸው!
“ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን፦ ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን) አታጋራ፤ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና ያለውን (አስታውስ)።”[31፥ 13]
2.ለወላጆቻቸው በጎ እንዲያደርጉ፤ አላህን እና ወላጆቻቸውን ላደረጉላቸው መልካም ነገር ማመስገን እንደሚገባቸው አስተምሯቸው።
“ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ ) በጥብቅ አዘዝነው፤ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው፤ ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው፤ ለኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት (አዘዝነው)፤ መመለሻው ወደኔ ነው።” [31፥ 14] 
3.አላህ ሁሉን አዋቂ እንደሆነና እንደሚቆጣጠረን አስተምሯቸው!
“(ሉቅማንም) አለ ፦ ልጄ ሆይ! እርሷ የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ብትሆንና በቋጥኝ ውስጥ ወይንም በሰማያት ውስጥ ወይንም በምድር ውስጥ፣ ብትሆን፣ አላህ ያመጣታል፤ አላህ ርኅሩኅ ውስጥ ዐዋቂ ነውና።” [31፥ 16]
4.ሰላትንም እንዲሰግዱ አስተምሯቸው።
“ልጄ ሆይ! ሰላትን አስተካክለህ ስገድ፤ በበጎ ነገርም እዘዝ፤ ከሚጠላም ሁሉ ከልክል፤ በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገሥ፤ ይህ በምር ከሚይያዙ ነገሮች ነው።” [31፥ 17] *********
ሀሳብ እና አስተያይትዎን ያጋሩን!
*********
ይወዳጁን!
telegram – https://t.me/lubnakids1
facebook – fb.me/lubnakids1
Instagram – https://www.instagram.com/lubnakidscorner/
Blog – https://lubnakidscorner.wordpress.com


Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started